Saturday, August 18, 2018

#በወንጌል_አላፍርም





#የዝማሬ_አምልኮ እና #ስብከት_አገልግሎት_ከአዲስ_አበባ_ስታዲያም
ይህን ይጫኑት፤ https://goo.gl/QgrPN4 በቀላሉ ሳብስክራይብ በማድረግ ከይቲዩብ መከታተል ይችላሉ፡፡ ሼር ያድርጉ፡፡

••በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም••

የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ስለማይጸድቅ በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል በጸጋው ይጸድቁ ዘንድ እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፡፡ ይህን ያደረገው በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጽድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት ሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ይመላለሳሉ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ ያወጣል። አሜን
(ሮሜ 3፡20፤ 8፡1-2 በተጨማሪ አንብቡ፡፡)
ቪዲዮን ለመመልከት https://goo.gl/QgrPN4 ይጫኑት፡፡

Friday, August 17, 2018

#የጌታ_እራት - #ይህን_ለመታሰቢያዬ_አድርጉት_አለ።


እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ለእናንተ የተሰጠ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያ አድርጉት፡፡ ጽዋውንም አንስቶ ይህ ስለ ብዙዎች የፈሰሰ የኃጢአት ስርየት የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፡፡ ሁላችሁም ከዚህ ጠጡ… ይህንን ባደረጋችሁ ጊዜ ሁሉ ለመታሰቢያ አድርጉት፡፡ (ማቴ 26፤26-29፤ ማር 14፡22-25፤ ሉቃ 22፡17-20፤ 1ኛ ቆሮ 11፡23-25)፡፡
በጌታ እራት ውስጥ የኢየሱስን ሞትንና ያደረገልንን እንድናስብ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በደሙ ያደረገልንን ነገር ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ እርሱ ሥራ ውስጥ ጽድቅን አግኝተናል፤ ቤዛነትንና ይቅርታን አግኝተናል፤ መንጻት ሆኖልናል፤ ወደ ምህርት መግባት ሆኖልናል እንዲሁም ድል ማድረግ ተሰጥቶናል፡፡ የመንግስቱ ወራሽ ያደረገን እግዚአብሔር ይመሰገን!
ፕረዘንስ ቲቪ ቻናል
ለቀጥታ ስርጭት https://goo.gl/qgrpn4 ይጫኑት፡፡

Monday, August 13, 2018

የወንጌል ጥሪ - ኢየሱስ ክርስቶስ ይወድሃል!




ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና  ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ኃጢአትም በአንድ ሰው ባለመታዘዝ ምክንያት ወደ ዓለም ገባ፡፡ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፡፡ ይህም በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፡፡ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፡፡ ነገር ግን ጠላቶች ሳለን እግዚአብሔር  በልጁ  ሞት በኩል አስታረቀን፡፡ ስለዚህ በአንዱ በአዳም በደል ምክንያት ሞት  በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። ይህም የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። የወንጌልን ጥሪ ለተቀበሉት ሁሉ በስሙም ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ለወንጌል ጥሪ ምላሽ የሚሰጥ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡ ይህ ጥሪ በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። የእምነት ቃሉም እንዲህ የሚል ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና፡፡ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ሮሜ 5፡6-21፤ ሮሜ 6፡1-23፤ ሮሜ 10፡8-11 ዮሐ 3፡18፤ 2ኛ ጴጥ 3፡9፡፡ በተጨማሪ አንብቡ፡፡  ለመመልከት https://goo.gl/qgrpn4 ይጫኑት፡፡

PRESENCE TV CHANNEL WORLDWIDE: በወንጌል አላፍርም

PRESENCE TV CHANNEL WORLDWIDE: በወንጌል አላፍርም: የዝማሬ አምልኮ እና ስብከት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ስታዲያም ይህን ይጫኑት፤ https://goo.gl/QgrPN4   በቀላሉ ሳብስክራይብ በማድረግ ከይቲዩብ መከታተል ይችላሉ፡፡ ሼር ያድርጉ፡፡

በወንጌል አላፍርም


የዝማሬ አምልኮ እና ስብከት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ስታዲያም
ይህን ይጫኑት፤ https://goo.gl/QgrPN4  በቀላሉ ሳብስክራይብ በማድረግ ከይቲዩብ መከታተል ይችላሉ፡፡ ሼር ያድርጉ፡፡

ምስክርነት





እህታችን ገነት ትባላለች፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት በጠላት እስራት ውስጥ ሆኜ ሰውነቴን ማዘዝ አልችልም ነበር ፡፡ እንደጤናማ ሰው የዕለት ተግባራትን ማከናወን አለመቻሌ ትልቅ ስቃይ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ኢየሱስ ፈዋሽ አምላክ ነው፡፡ በአስደናቂ ሁኔታ ኢየሱስ ነፃ አወጣኝ፡፡ ሙሉ ምስክርነቱን ለመመልከት https://goo.gl/qgrpn4 ይጫኑት፡፡