ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ኃጢአትም በአንድ ሰው ባለመታዘዝ ምክንያት ወደ ዓለም ገባ፡፡ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፡፡ ይህም በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፡፡ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፡፡ ነገር ግን ጠላቶች ሳለን እግዚአብሔር በልጁ ሞት በኩል አስታረቀን፡፡ ስለዚህ በአንዱ በአዳም በደል ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። ይህም የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። የወንጌልን ጥሪ ለተቀበሉት ሁሉ ፥
በስሙም ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ለወንጌል ጥሪ ምላሽ የሚሰጥ ሁሉ የእግዚአብሔር
ልጅ ይባላል፡፡ ይህ ጥሪ በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። የእምነት ቃሉም እንዲህ የሚል ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና፡፡
ለአንዳንዶች
የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ሮሜ 5፡6-21፤ ሮሜ 6፡1-23፤
ሮሜ 10፡8-11 ዮሐ 3፡18፤ 2ኛ ጴጥ 3፡9፡፡ በተጨማሪ አንብቡ፡፡ ለመመልከት https://goo.gl/qgrpn4 ይጫኑት፡፡
No comments:
Post a Comment