Saturday, August 18, 2018

••በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም••

የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ስለማይጸድቅ በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል በጸጋው ይጸድቁ ዘንድ እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፡፡ ይህን ያደረገው በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጽድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት ሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ይመላለሳሉ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ ያወጣል። አሜን
(ሮሜ 3፡20፤ 8፡1-2 በተጨማሪ አንብቡ፡፡)
ቪዲዮን ለመመልከት https://goo.gl/QgrPN4 ይጫኑት፡፡

No comments:

Post a Comment