Sunday, August 12, 2018

#በአባቴ_ቤት_ብዙ_መኖሪያ_አለ፤

በፎግራፍ የምትመለከቱትን ቦታና ሀውልት በእስራኤል የሆምሌስ/HOMELESS/ ጂሰስ/ኢየሱስ/ ማደሪያው ነው ይባላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ስለራሱ እንዲህ ብሎአል፦ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው። በዚህ ቋሚ ሀገር የለንም፤ ሀገራችን በላይ በሰማይ ነው፡፡ ኢየሱስን እንዲህ ብሎ አስተምሮናል፡፡ "ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና። ማራናታ!

No comments:

Post a Comment