እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ለእናንተ
የተሰጠ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያ አድርጉት፡፡ ጽዋውንም አንስቶ ይህ ስለ ብዙዎች የፈሰሰ የኃጢአት ስርየት የአዲስ ኪዳን ደሜ
ነው፡፡ ሁላችሁም ከዚህ ጠጡ… ይህንን ባደረጋችሁ ጊዜ ሁሉ ለመታሰቢያ አድርጉት፡፡ (ማቴ 26፤26-29፤ ማር 14፡22-25፤ ሉቃ
22፡17-20፤ 1ኛ ቆሮ 11፡23-25)፡፡
በጌታ እራት ውስጥ የኢየሱስን
ሞትንና ያደረገልንን እንድናስብ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በደሙ ያደረገልንን ነገር ተቆጥሮ አያልቅም፡፡
እርሱ ሥራ ውስጥ ጽድቅን አግኝተናል፤ ቤዛነትንና ይቅርታን አግኝተናል፤ መንጻት ሆኖልናል፤ ወደ ምህርት መግባት ሆኖልናል እንዲሁም
ድል ማድረግ ተሰጥቶናል፡፡ የመንግስቱ ወራሽ ያደረገን እግዚአብሔር ይመሰገን!
ፕረዘንስ ቲቪ ቻናል
No comments:
Post a Comment